ጊፍት ሪል ስቴት በመንደር 3 የመኖሪያና የንግድ አፓርትማዎችን አስመረቀ

ላለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ዘመናዊ የመኖሪያ ቪላ መንደሮችን በመገንባት በቂ ልምድ ያካበተው ጊፍት ሪል እስቴት፣ በተለምዶ ፈረስ ቤት ተብሎ በሚጠራው እና ደራርቱ ቱሉ አደባባይ አጠገብ የገነባቸውን ረጃጅም፣ ዘመናዊ የመኖሪያና የንግድ አፓርትማዎችን አስመረቀ፡፡

ይህ የጊፍት ሪል ስቴት መንደር ሦስት 54ሺህ ሜትር ካሬ ላይ ያረፈ ሲሆን ወለላቸው ከ2-24 የሚደርሱ ፎቆችን ያካተተ አፓርትማዎች፣ ቪላዎች፣ ታዎን ሃውሶችና ሮው ሃውሶችን የያዘ በአጠቃላይ 3700 ቤቶችን የያዘ መንደርእንደሆነ ተገልጿል።

ከዚህ በፊት ጊፍት ሪል እስቴት የካ እና ሲኤምሲ ላይ በተለምዶ የጊፍት መንደር አንድና መንደር ሁለት ተብለው በሚታወቁ የመኖሪያ አካባቢዎች፣ 95 ሺህ ካሬ መሬት ላይ ዘመናዊ መንደሮችን ገንብቶ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡

ጊፍት ሪል እስቴት በቀጣይ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የ12 ሺህ ቤቶች ግንባታ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር የ4 ሺህ ቤቶች ግንባታ ስራ በለገሃር አካባቢ እየተፋጠነ ይገኛል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *