ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ጊፍት ሪል ስቴት ኃ.የተ.የግ.ማህበር በሀገራችን የሪል ስቴት ኢንደስትሪ ግንባር ቀደም ድርጅት ሲሆን ከፍተኛ ጥራትና ማራኪ ዲዛይን ያላቸው የተለያዩ ቤቶችን እና አፓርትመንቶቹን በመገንባት በደምበኞች ዘንድ ተመራጭ የሆነ ድርጅት ሲሆን ለበርካታ አመታት የጥራት እና የውበት ምልክት ሆኖ የዘለቀ የግዙፉ የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ አባል ነው፡፡

ድርጅታችን ጊፍት ሪል እስቴት ኃ.የተ.የግ ማህበር በሪል እስቴት ሽያጭ ሥራ ግንባር ቀደም ሲሆን የዚህ የሽያጭ ሀይል አባል ሆነው ራሳቸውን ለመለወጥ እና የፕሮፌሽናሊዝም ህይወታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚሹ፣ነዋሪነታቸዉ በድሬደዋ፣ በጂግጂጋ፣ በሐረር፣ በአዳማ፣ በመቀሌ፣ በሐዋሳ፣ በጅማ ፣ በሆሳዕና፣ በወራቤና በሌሎች የክልል ከተሞች የሆኑ ብቁ፣ በአከባቢዉ የስራ ቋንቋ መግባበት የሚችሉ  እንዲሁም ከዚህ በታች የተቀመጠዉን መስፈርት የሚያሟሉ የሽያጭ ባለሙያዎችን አወዳድሮ በየጊዜዉ በሚታደስ ኮንትራት ዉል ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡  

የስራ መደቡ መጠሪያ – የክልል የሽያጭ ተወካይ (Regional sales representative)

የትምህርት ደረጃ –   በዲፕሎማ ወይም በደረጃ-3 በማርኬቲንግ፣ በሴልስ፣ በኢንተርናሽናል ትሬድ እና በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የተመረቀ/ች፣ የብቃት ማረጋገጫ (COC) ምዘና ዉጤት እና የንዋሪነት መታወቂያ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የቅጥር ሁኔታ –     በኮንትራት (እንደ ዉጤታማነቱ በየ3 ወሩ የሚታደስ)

ደመወዝ –          በድርጅቱ እስኬል መሰረት እና ከእያንዳንዱ የአፓርታማ፣ ሱቅ እና ሌሎች የቤት ዓይነቶች ሽያጭ የሚከፈል ማራኪ ኮሚሽን

ጾታ –             አይለይም

ብዛት-             150.00 (አንድ መቶ ሐምሳ)

የስራ ልምድ –    0 ዓመት ሆኖ በሽያጭ ሠራተኝነት የሥራ ልምድ ያለዉ/ላት ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

ተፈላጊ ክህሎት –   ጠንካራ የስራ ባህል፣ጥሩ የተግባቦት ክህሎት፣ ከለውጦች ጋር በፍጥነት የመላመድ፣ የደምበኞችን ፍላጎት የመለየትና የላቀ የጊዜ አጠቃቀምና  ያለው/ያላት፡፡

ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች የማይመልስ የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን በመያዝ አዲስ አበባ ቦሌ መንገድ ጌቱ ኮሜርሻል ፊት ለፊት በሚገኘዉ የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ባህር ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803 በአካል በመቅረብ ወይም በኢሜይል አድራሻ giftrealestatehr2020@gmail.com ወይም ፖ.ሳ.ቁ 2522 ወይም በዌብ ሳይት https://giftbusinessgroup.com/job-openings/ በመላክ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7(ሰባት) ተከታተይ የሥራ ቀናት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር. 011465558, 0114671975,

ጊፍት ሪል እስቴት

ማህበረሰብ እንገነባለን!

Job Category: Marketing
Job Type: Freelance

Apply for this position

Allowed Type(s): .pdf, .doc, .docx