“ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት ማጠናቀቅ የሚያስችል አቅም ፈጥረናል” አቶ ገ/የሱስ ኢጋታ – የጊፍት ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ

የጊፍት ሪል ስቴት ማኔጅመንት የሪል ስቴቱ መንደር ሶስት ፕሮጀክት ምረቃ አስመልክቶ የምስጋና መርሃ ግብር አዘጋጅቷል፡፡

በመርሃ ግብሩ ወቅት የጊፍት ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገ/የሱስ ኢጋታ መንደሩ ተጠናቆ ለምረቃ እንዲበቃ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው አያይዘውም በዚህ ፕሮጀክት የተገኘውን ልምድና ተሞክሮ በመውሰድ ግንባታዎችን በፍጥነትና በጥራት ማጠናቀቅ የሚያስችል አቅም ፈጥረናል ብለዋል፡፡

የማኔጅመንት አባላት በበኩላቸው ጊፍት በአሁኑ ወቅት ግንባታዎችን በሚፈለገው ደረጃ ማጠናቀቅ የሚያስችል የሰለጠነ ባለሙያና ቁሳቁስ መኖሩን ተናግረዋል፡፡

በግንባታ ላይ ያሉትን ፕሮጀክቶችንም በተያዘላቸው ውል መሰረት በማጠናቀቅ ለማስመረቅ ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *