ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ በጥራት እንዲጠናቀቁ ግብዓቶችን በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ የጊፍት ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ አሳሰቡ፡፡

ጊፍት ሪል ስቴት በግንቦት ወር በተከናወኑ ዓብይት የስራ አፈጻጸሞች ላይ ከስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱም ግንባታዎችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ የ24 ሰዓት ሽፍት መርሃ ግብር ወጥቶ ወደስራ ለማስገባት የምሽት ስራ መጀመሩ ተገልጾ ወደሙሉ ትግበራ ለመግባት በግብዓትና ሰው ሀይል የሚታየውን ማነቆ መቅረፍ ይገባል ተብሏል፡፡

ግንባታዎችን በተቀመጠው የጥራት ደረጃ መሰረት ለመገንባት የተደረገው ጥረት አበረታች መሆኑ ተገልጾ በቀጣይ ከዚህ የተሻለ አፈጻጸም እንዲመዘገብ ጥራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት ተመላክቷል፡፡

የጊፍት ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ በጥራት እንዲጠናቀቁ ግብዓቶችን በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸው ችግሩን ለመቅረፍ ከዕቃ አቅራቢዎች ጋር የተጀመረው ግንኙነት ሊጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም በቀጣይ ወር ከዚህ የተሻለ አፈጻጸም እንዲመዘገብ የግብዓትና ፋይናንስ አቅርቦትን ማሻሻል እንዲሁም የኮንትራክተሮች የአቅም ውሱንነት ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡

በውይይቱም በሚያዝያ ወር አፈጻጸሞች በተሰጡ አስተያየቶች የታዩ ለውጦች ቀርበው ቤቱ ውይይት አድርጎባቸዋል፡፡

መረጃው፡- በጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው

ለበለጠ መረጃ፡-

በድረገጽ: https://www.giftbusinessgroup.com                                                                                             

በቲዊተር: https://twitter.com/GIFTBusinessG                                                     

በዩቲዩብ: https://www.youtube.com/channel/UCcqr7cpVv9ski-F7haxXx4w                                                                                                    በፌስቡክ: https://www.facebook.com/profile.php?id=100090918391017&mibextid=ZbWKwL                                                         በቴሌግራም: https://t.me/giftbusinessgroup

ይጠቀሙ፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *