ጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ – እርስ በርስ ተሰላስለው ለስኬት የበቁ ኩባንያዎች ተምሳሌት

ጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ በመዲናችን አዲስ አበባ ብሎም በሀገራችን ያለውን የገበያ ፍላጎት ለማርካት በሚደረገው ጥረት በልዩ እውቀትና በአርቆ አሳቢነት የተዋሃዱ በስኬት የሚመሩ የንግድ ድርጅቶች ጥምረት ነው።

ለጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ መፈጠር ምስረታውን እ.እ.አ. በ1990 ያደረገው ጊፍት ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ኩባንያ ፈር ቀዳጅ ሲሆን የተለያዩ ምርቶችን ወደውጭ በመላክና ወደሀገር ውስጥ በማስገባት  ተቀባይነትን ያገኘ አንጋፋ ኩባንያ ነው፡፡

እሱን ተከትሎ የብረታብረት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ኩባንያ ምስማሮችን፣ ሽቦዎችን እና የተለያዩ ብረትና ብረት ነክ የሆኑ ምርቶችን በማምረት ለገበያ ተደራሽ በማድረግ እ.እ.አ. በ2000 ተቋቁሟል፡፡

ከዚያም በሀገራችን ያለውን የቤት ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ ጥራት ያለው ቤት ማቅረብ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት እ.እ.አ. በ2005 ጊፍት ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ ሊመሰረት ቻለ፡፡ በአሁኑ ወቅትም በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች ቪላዎችን እና አፓርታማዎችን በመገንባት በአጭር ጊዜ በሪል ስቴት ገበያ ጥሩ ስምና ዝናን ማትረፍ ችሏል።

በመቀጠልም የሪል ስቴት ገበያ ዕድገትን ተከትሎ ጊፍት ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ እ.እ.አ. በ2006 የተመሰረተ ሲሆን የህንጻና መንገድ ኮንስትራክሽን ስራዎችን በጥራትና በብቃት በመገንባት እውቅና እያገኘ ይገኛል፡፡

እንዲሁም ጊፍት የህንጻ ቁሳቁስ ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ ከብረት፣ ከአልሙኒየም እና ከእንጨት የተሰሩ የህንጻና ኮንስትራክሽን ቁሳቁሶችን በማምረት ለጊፍት ሪል ስቴትና ሌሎች ድርጅቶች በማቅረብ እ.እ.አ. 2000 የተቀላቀለ ኩባንያ ነው፡፡

እነዚህ ኩባንያዎች እርስ በርስ ተሰላስለው ለሌሎች ኩባንያዎች ተምሳሌት የሚሆን ስኬት እያስመዘገቡ ይገኛል፡፡ ለዚህም ውጤት የድርጅቱ ባለቤትና ማኔጅመንት አባላት የተናበበ አመራር እንዲሁም የመላ ሰራተኞች ትጋት የላቀ ሚና ተጫውቷል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *