ጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ለመቄዶኒያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ

ተቋሙ ያደረገውን የገንዝብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለመቄዶኒያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል መሥራች የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ዛሬ አስረክበዋል።

በዚህም የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ማኔጅመንትና ሠራተኞች የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ 3 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የምግብ፣ አልባሳትና የዕርድ ከብት አበርክተዋል።

የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ድርጅቱ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው።

ለመቄዶኒያ የተደረገው ድጋፍ የተቋሙ ሠራተኛ ከማኔጅመንቱ ጋር በመሆን ያደረገው መሆኑን ጠቁመው ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የመቄዶኒያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል መሥራች የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ በዚህ ወቅት ጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል።

ይህንን አርአያነት ያለው ተግባር በመከተል ሌሎችም አካላት ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *