ጊፍት ቢዝነስ ግሩፕን እና ሌሎች 140 የዓውደርይ አቅራቢዎች የሚሳተፉበት ዓውደርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ

ጊፍት ቢዝነስ ግሩፕን እና ሌሎች 140 የዓውደርይ አቅራቢዎች የሚሳተፉበት “ቢግ 5 ኮንትራክት ኢትዮጵያ” ዓውደርዕይ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በይፉ ተከፍቷል።

ዓውደርዕዩ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን የግንባታው ዘርፍ ዕድሎችንና አማራጮችን በመጠቆም፣ በዘርፉ የተሰማሩ ግብዓት አቅራቢዎች በተለያዩ ግዙፍ ግንባታዎች ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉና የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉም ምቹ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ተነግሯል።

በዚህ ዓውደ ርዕይ ላይ የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ አጋር የሆነው የራሽያ ኩባንያም የፋይበርግላስ ቴክኖሎጂን ለታዳሚዎች እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡

ዛሬን ጨምሮ ለሦስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዓውደርዕዩ ከ24 አገራት የተውጣጡ ከ140 በላይ የኢግዚቢሽን አቅራቢዎች ይሳተፋሉ፡፡

የሚቆየው ይህ ዓውደርዕይ አዳዲስ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ውጤቶችን ለዕይታ የሚቀርቡበት ሲሆን፤ የታዳምያንን ትኩረት በመሳብ በኢትዮጵያን የግንባታ ኢንደስትሪ ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡

ከ6 ሺሕ በላይ በሕንጻ ንድፍ እና በግንባታ ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች፣ የሕንጻ ጥገናና የንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የዘርፉ አካላት እንዲሁም የዘርፉ ልሂቃን በአንድ የሚገናኙበት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *