ጊፍት ሪል እስቴት በመሃል አዲስ አበባ ዘመናዊ፣ ቅንጡ የመኖሪያና የንግድ አፓርትማ መንደሮች ግንባታ አስጀመረ፡፡

ጊፍት ሪል እስቴት በመሃል አዲስ አበባ ዘመናዊ፣ ቅንጡ የመኖሪያና የንግድ አፓርትማ መንደሮች ግንባታ አስጀምሯል፡፡

ሪል እስቴቱ በአይነቱ የመጀመሪያ በሆነው እና በመንግስትና የግል አጋርነት ልማት ፕሮግራም መሠረት፣ 12 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ስምምነት የፈረመ ሲሆን በዛሬው ዕለት የዚህ ፕሮግራም የመጀመሪያው ዙር ሊገነባ የታቀደው የ4 ሺህ ቤቶች ግንባታ የማስጀመር ስነሥርዓት፣ የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በይፋ ተካሂዷል፡፡

በላቀ ጥራትና ዘመኑን በዋጀ የቴክኖሎጂ ድጋፍ የሚገነቡ 3 ሺህ 540 የመኖሪያ፣ 460 የሱቅ፣ ባጠቃላይ ከ4 ሺህ በላይ ቤቶች ሲኖሩት፣ ትምህርት ቤትና ሌሎች ማህበራዊና ማህበረሰባዊ መገልገያዎችን የሚያካትት ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ ግንባታ በሶስት ዓመት ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

በአይነቱ የመጀመሪያው በሆነው በግል ሪል እስቴትና በመንግስት አጋርነት የሚገነባው ይህ የመኖሪያ መንደር ከፍታቸው ከ14 እስከ 22 የሚሆኑ ፎቆች ይኖሩታል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ግንባታ እንደተጋመሰ በሁለተኛ ዙር ለሚገነቡ ተጨማሪ 8 ሺህ ቤቶችና የንግድ ማዕከላት ጊፍት ሪል እስቴት ከእህት ኩባንያዎቹና ዓለም ዓቀፍና አገር አቀፍ አጋሮቹ ጋር በዲዛይን፣ ቴክኖሎጂና ፋይናንስ የቅድመ ዝግጅት ሥራ በመስራ ላይ ይገኛል፡፡

ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሩ አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ አካላት በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ከማስቻሉም በላይ የመንደሩ ኗሪዎች በተሻለ እና ጤናማ በሆነ አካባቢ እንዲኖሩ የሚያስችል ከባቢና፣ ለበርካታ ዜጎቻችን የስራ ዕድል ይፈጥራል፡፡

የከተማችን እምብርት ላይ የሚገነባ መንደር በመሆኑም አስተማማኝ የሜትሮፖሊታን ድባብ የተላበሰ ዘመናዊ የጊፍት ሪል እስቴት መንደር ይሆናል፡፡

ጊፍት ሪል እስቴት ከሁለት አሥርተ አመታት በላይ ዘመናዊ የመኖሪያ ቪላ መንደሮችን በመገንባት በቂ ልምድ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በፈረስ ቤት አካባቢ የገነባቸውን ረጃጅም ዘመናዊ የመኖሪያና የንግድ አፓርትማዎችን በቅርቡ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *