ጊፍት ሪል ስቴት ጠመንጃ ያዥ ትምህርት ቤትን ለማደስ ቃል መግባቱ ተገለጸ

ጊፍት ሪል ስቴት በመዲናዋ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጠመንጃ ያዥ አንደኛና መካከለኛ ትምህርት ቤትን ለማደስ ቃል መግባቱ ተገለጸ፡፡

የጊፍት ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገ/የሱስ ኢጋታ እና ሌሎች የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አመራሮች ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የጊፍት ሪል ስቴት ስራ አስፈጻሚ አቶ ገ/የሱስ ኢጋታ ሪል ስቴቱ የሀገሪቱን ልማት በሚያረጋግጡና የዜጎችን ሕይወት የሚቀይሩ ሥራዎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

ትምህርት ቤት እውቀትንና ክህሎትን ከማስጨበጥ ባለፈ ተማሪዎች በመልካም ሥነ-ምግባር ታንጸው እንዲወጡ የሚያስችል በመሆኑ ሪል ስቴቱ ለጠመንጃ ያዥ ትምህርት ቤት እድሳት ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። 

የትምህርት ቤቱ እድሳት ለተማሪዎችና ለመምህራን ምቹ የመማር ማስተማር ሁኔታ በመፍጠር የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እንደሚያስችልም ገልጸዋል።

ጊፍት ሪል ስቴት በዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖሩ ዜጎች ቤት በመገንባት፣ በአረንጓዴ ልማት፣ ለተፈናቀሉ ዜጎች ደጋፍ በማድረግ፣ በትምህርት ቤት እድሳት፣ ምገባና ቁሳቁስ በማሟላት እንዲሁም በተለያዩ መስኮች ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *