ጊፍት ሪል ስቴት የድርጅቱን የብራንድ አምባሳደር ለህዝብ በይፋ አስተዋወቀ

ጊፍት ሪል ስቴት የድርጅቱን የብራንድ አምባሳደር ለህዝብ በይፋ አስተዋወቀ

***********

ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ በሪል ስቴት ኢንዱስትሪ በዘላቂነት የቆየው ጊፍት ሪል ስቴት የብራንድ አምባሳደሩን ይፋ አድርጓል፡፡

የጊፍት አምባሳደር ጊፍት ሪል ስቴት በሽያጭ እና በማርኬቲንግ ሙያተኞቹ የሚያከናውናቸው መጠነ ሰፊ ሽያጭና ደንበኞችን የማፍራት ተግባራትን በተሳለጠ አግባብ ያግዛል፡፡

ጊፍት ታዋቂውን የኪነጥበብ እና የሚዲያ ሰው አብርሃም ወልዴን ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የድርጅቱ አምባሳደር አድርጎ ውል ተፈራርሞ በመሰየሙ የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ በጊፍት ደንበኞች፣ ቤተሰቦችና አጋሮች ስም ይገልፃል፡፡

የጊፍት ሪል ስቴት አምባሳደርም ይህንን አዲስ የጊፍት አቅጣጫ በዛሬው ዕለት ውል በመፈራረም ማስተዋወቅ የሚጀምርበት እለት ነው፡፡

የጊፍት አምባሳደር አብርሃም ወልዴም ጊፍት “ማህበረሰብን እንገነባን!” በሚል መሪ ቃል በሪል ስቴት ኢንዱስትሪው ውስጥ በፅናት ከፍተኛ ሚና በመጫውት ላይ ለሚገኘው ድርጅታችን ለሚያደርገው ያላሰለሰ አምባሳደራዊ አበርክቶ መልካሙን ከአደራ ጭምር ይመኛል፡፡

የብራንድ አምባሳደራችን በስነጥበቡ እና በሚዲያው አለም በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር ዝናን እየተጎናፀፈ በመምጣት በዘርፉ ታዳጊ ተተኪዎችን በማስተማር፣ በመኮትኮት እና በማፍራት ይታወቃል፡፡

ድርጅታች ታዋቂው የፊልም እና የሙዚቃ ፕሮዲዩሰር፣ በአገራችን ባህል እና ወግ የተቃኘ፣ አልፎ ተርፎም የአገራችንን ኪነጥበባዊ እሴቶች ከአለም አቀፉ የዘርፉ ሙያ ጋር እንዲጣጣም የራሱን አሻራ በማሳረፍ ላይ የሚገኝ አመለ ሸጋ እና መልካም ዜጋ ነው፡፡

የአሁንና የወደፊት ደንበኞቻችን! የጊፍት አምባሳደራችሁ አብርሃም ወልዴ፣ የጊፍትን ብራንድ በማስተዋወቅ፣ ዘመናዊ  የጊፍት መንደራችን በሙሉ ኩራትና በእኛነት ስሜት ለማስተዋወቅ አብርሃም ወልዴ ለሚያደርገው ጥረት ትብብራችሁ የማይለየው እንደሚሆን ፅኑ እምነት አለን፡፡

ጊፍት እስከ አሁን ባደረገው ጉዞ፣ ከ150 ሺህ ካሬ በላይ በሆነ ቦታ ላይ ሶስት ዘመናዊ መንደሮችን በሲኤም ሲ እና ፈረስ ቤት አካካቢ ገንብቶ አስረክቧል፡፡

የልማት ግስጋሴውን በመቀጠል፣ በአዲስ አበባ እምብርት በቦሌ፣ በአትላስ፣ በለገሃር፣ በ22፣ በስድስት ኪሎ፣ በተክለኃይማኖትና በፊጋ አካባቢዎች ዘመኑን የዋጁ ወለላቸው ከ20 በላይ የሆኑ ዘመናዊ መንደሮችን፣ የንግድ እና የመኖሪያ አፓርትማዎች እና ሞሎችን ግንባታ እና ዲዛይን ጀምሯል፡፡

አብዛኞቹ በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቁ  ሲሆን ሽያጭም ተጀምሯል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *