ጊፍት ሪል ስቴት ከአቤም እስከ አሜሪካ ሜዲካል ሴንተር የሚገኘውን የመንገድ አካፋይ በአረንጓዴ የማስዋብ ስራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ጊፍት ሪል ስቴት ከአቤም እስከ አሜሪካ ሜዲካል ሴንተር የሚገኘውን 13 ሺህ ካሬ ሜትር የመንገድ አካፋይ በአረንጓዴ የማስዋብ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡

ሪል ስቴቱ የከተማውን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የአረንጓዴ ልማት ስራ እየሰራ ሲሆን በዚህ ስፍራ 17 ሺህ 800 ጀራንየም፣ 12 ሺህ ቨርቨና አበባ፣ 5 ሺህ ድንች አበባ፣ 5 ሺህ ፒከስ፣ 3 ሺህ የወፍ ቆሎ እና 200 ቱያ በመተከል ላይ ናቸው፡፡

በተጨማሪም ሪል ስቴቱ አካባቢውን በ3 ሺህ 500 ቴራዞ፣ 48 ሜትር ኩዩቢክ አሸዋ እና 36 ሜትር ኩዩቢክ ቀይ አሸዋ የማደስ ስራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ሪል ስቴቱ በሚሰራው ስራ ላይ የአበባ፣ ችግኝና ቁሳቁስ አቅርቦት፣ የዲዛይን ስራ፣ የማማከር እና የሰው ሃይል እገዛዎችን እያደረገ ሲሆን ቦታውን በአረንጓዴ የማልማት  ስራውን በአንድ ሳምንት ውስጥ በማጠናቀቅ ለማስመረቅ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነም ይገኛል፡፡

ጊፍት ሪል ስቴት አዲስ አበባን እንደስሟ አዲስ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች በአረንጓዴ በማስዋብ ስራ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *