ጊፍት ሪል ስቴት ለአቅመ ደካሞች ያስገነባውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለከተማ ከንቲባዎችና ርዕሰ መስተዳደሮች አስጎበኘ

ጊፍት ሪል ስቴት ለአቅመ ደካሞች ያስገነባውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለከተማ ከንቲባዎችና ርዕሰ መስተዳደሮች አስጎብኝቷል፡፡

ከ200 በላይ የከተማ ከንቲባዎች እና ርዕሰ መስተዳድሮች በመዲናዋ የተሰሩ ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

የጊፍት ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ ጊፍት ሪል ስቴት ከእህት ኩባንያዎች ጋር በመተባበር ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ እንዲሁም በተለያዩ ሀገራዊ ጥሪ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከነዚህ ማህበራዊ ኃላፊነቶች መካከል የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለመቅረፍ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸው በመዲናዋ ለሚኩራ ክፍለከተማ የተገነቡ 40 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ማስተላለፉን ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በሌሎች ከተሞችም የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ገብረየሱስ አስታውቀዋል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ አምስት ወለሎች ያሉት ሲሆን እስከ 70 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎባቸዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *