ጊፍት ሪል ስቴት ለልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል 800 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ጊፍት ሪል ስቴት በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ለልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል 800 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የሪል ስቴቱ ማኔጅመንትና ሰራተኞች በየወሩ ከደመወዛቸው ያዋጡትን 600 መቶ ሺህ ብር እንዲሁም የጊፍት ሪል ስቴት ባለቤትና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ በግላቸው 200 መቶ ሺህ ብር ለማዕከሉ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ወቅት የሪል ስቴቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ ሪል ስቴቱ በየዓመቱ ከድርጅቱና ከሰራተኞች ደመወዝ በየወሩ በማዋጣት በልብ ህመም ለሚሰቃዩ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ሪል ስቴቱ የዜጎችን ችግር ማቃለል በሚያስችሉ የተለያዩ መስኮች ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸው በቀጣይም ከህዝብ የተገኘን ሀብት መልሰን ለህዝብ በማዋል በመልካም ስራ ላይ ትኩረት አድርገን እንሰራለን ብለዋል፡፡

በዕለቱ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤናና የስኬት እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሰራተኞችም በበኩላቸው ለልብ ህሙማን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *