የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ሰራተኞች በ6ኛው ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ አከናወኑ

የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ቃል በለሚ ኩራ ከተማ ክፍለ ከተማ የጊፍት ሪል ስቴት መንደር ሶስት አካባቢ የችግኝ ተከላ አከናውነዋል።

በመርሃ ግብሩ 5 ሺህ ሀገር በቀል ችግኞች የተተከሉ ሲሆን ከጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ሰራተኞች በተጨማሪ የአካባቢው ማህበረሰብም ተሳትፈዋል።

የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ በመርሃ ግብሩ ወቅት እንደተናገሩት የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ሰራተኞች በየአመቱ በችግኝ ተከላ ላይ በንቃት በመሳተፍ ለሌሎች አርአያ በመሆን ቆይተዋል።

አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሀገራችንን ከፍታ ለማረጋገጥ ታቅዶ በመተግበር ላይ መሆኑን አቶ ገብረየሱስ ገልጸው መላ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት በንቃት በመሳተፋቸው ምስጋና አቅርበዋል።

የተተከሉ ችግኞችንም በመንከባከብ ለታቀደው ዓላማ እንዲውል የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ የተሳተፉ ሰራተኞች በበኩላቸው የሀገርን ልዕልና በልማቱ አስጠብቆ ለማስቀጠል ለአረንጓዴ ልማት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *