የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ማኔጅመንት አባላት በ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት አደረገ

ማኔጅመንቱ የቢዝነስ ግሩፑ እህት ኩባንያዎች የጊፍት ትሬዲንግ፣ የጊፍት ኮንስትራክሽን፣ የጊፍት ብረታብረት ማምረቻ እና የጊፍት ህንጻ መሳሪያ ማምረቻ ድርጅቶች የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርበው ውይይት አድርጎባቸዋል፡፡

በቀጣይ በጀት ዓመት የድርጅቶችን አቅም ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ የማኔጅመንት አባላት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በበጀት ዓመቱ ለሚጀመሩ አዲስ ፕሮጀክቶች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ በውይይቱ ተመላክቷል፡፡

የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ በቀጣይ በጀት ዓመት በእህት ድርጅቶች የተያዙ ዕቅዶች ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ዕቅዶችን በተያዘላቸው ዘመን ለማሳካት የስራ ተነሳሽነት በመጨመር ከመላ ሰራተኞች ጋር በቅንጅት መተግበር እንደሚያስፈልግ አቶ ገብረየሱስ አስረድተዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *