የጊፍት ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገ/የሱስ ኢጋታ በዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖሩ ዜጎች የጋራ መኖሪያ ህንጻ ግንባታአስጀመሩ

የጊፍት ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገ/የሱስ ኢጋታ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖሩ ዜጎች የጋራ መኖሪያ ህንጻ ግንባታ አስጀምረዋል፡፡

በዛሬው እለት የተጀመሩ ቤቶች አቅመ ደካሞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ባለ 5 ወለል ህንጻ፤ ለግንባታው 92 ሚሊዮን ወጪ የሚደረግ ሲሆን በሚቀጥሉት ሦስት ወራት የሚጠናቀቅ ነው።

የጊፍት ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገ/የሱስ ኢጋታ በግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ላይ እንደገለጹት፤ ሪል ስቴቱ መንግሥት ያቀረበውን ጥሪ ተቀብሎ ሃላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ የልማት መስኮች እየሰራ ነው ብለዋል።

አቶ ገብረየሱስ አያይዘውም በክፍለ ከተማው በሚቀጥሉት 90 ቀናት የነዋሪውን አንገብጋቢ የቤት ችግር ማቃለል የሚችል ባለ 5 ወለል ህንፃ ለ25 አባወራዎች የሚገነባ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ሪል ስቴቱ ከዚህ ቀደምም የተማሪዎች ምገባን ጨምሮ በቤት ግንባታና በሌሎችም በከተማዋ በሚደረጉ ፕሮጀክቶችና ማህበራዊ ኃላፊነቶች ላይ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸው፤ በቀጣይም ከመንግሥት ጎን ሆኖ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ በበኩላቸው ጊፍት ሪል ስቴት በዝቅተኛ ኑሮ ለሚገኙ ዜጎች የቤት ችግርን ለመቅረፍ ለሚያደርገው ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

በአንድ ጊዜ የሁሉንም ነዋሪዎች የቤት ችግር መቅረፍ ባይቻልም ከመንግስት ጋር በመቀናጀት ችግሩን ለማቃለል በሚደረገው ጥረት ጊፍት ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባና የቦሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች እንዲሁም የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ስራ አስፈጻሚዎች ተገኝተዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *