የጊፍት ሪል ስቴት ማርኬቲንግ ክፍል የሶስት ወራት አፈጻጸምን አስመልክቶ የዕውቅና እና ማበረታቻ ዝግጅት ተካሄደ፡፡

የጊፍት ሪል ስቴት ማርኬቲንግ ክፍል የሶስት ወራት አፈጻጸምን አስመልክቶ የዕውቅና እና ማበረታቻ ዝግጅት አካሂዷል፡፡

የማርኬቲንግ ክፍሉ በ2016 ሩብ አመት የዕቅዱን 140 በመቶ አከናውኗል፡፡

በመርሃ ግብሩ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገቡ የሽያጭ ኦፊሰሮች፣ ሽያጭ አስተባባሪዎች፣ የሽያጭ ስራ አስኪያጆች እንዲሁም የማርኬቲንግ ክፍሉ የደምበኞች ድጋፍ ኦፊሰር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በሩብ አመቱ አሉላ ዮሐንስ ከካዛንቺስ ሽያጭ ቢሮ በ1ኛ ደረጃ ኮከብ የሽያጭ ስራ አስኪያጅ ሆኖ ሲሸለም፣ ቤተልሔም ጌታቸው በኮከብ ሽያጭ አስተባባሪ እንዲሁም ቴዎድሮስ አለማየሁ በኮከብ ሽያጭ ኦፊሰር በ1ኛ ደረጃ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በየዘርፉ እስከ 3ኛ ደረጃ የወጡ ሰራተኞችም የዕውቅና ምስክር ወረቀት የተቀበሉ ሲሆን የደምበኞች ድጋፍ ኦፊሰር የሆኑት ወ/ሮ አዳነች አስፋው የደምበኞች ውል ዝግጅት ስራን በተቀላጠፈ ሁኔታ በመስራት የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *