እንኳን ለ1 ሺህ 445ኛው ኢድ- አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ማኔጅመንትና ሰራተኞች እንኳን ለ1 ሺህ 445ኛው ኢድ- አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታችን እንገልጻለን፡፡

የኢድ አል ፈጥር በዓል የእዝነትና የርህራሄ፣ የመተሳሰብ፣ ያለው ለሌለው በማካፈል በአብሮነት የሚያሳልፈው እና ማህበራዊ ግንኙነትን የበለጠ የሚያጠናከርበት በመሆኑ በተለይ በዚህ ወቅት መላው ህዝበ ሙስሊም በዓሉን በመደጋገፍ እና በመረዳዳት ሊያከብር እንደሚገባ እናምናለን።

በመሆኑ የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ማኔጅመንትና ሰራተኞች ከዚህ ቀደም በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ችግሮች የሌሎች ሰዎችን ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ስናደርግ የነበረውን የመረዳዳት ባህል በዚህ በዓልም የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በቅዱሱ የረመዳን ወር ሕዝበ ሙስሊሙ በጾም፣ በጸሎት፣ በመረዳዳት እና በመደጋገፍ ያሳለፈው መልካም እሴት በቀሪ ጊዜያትም ሊጠናከር ይገባል።

ኢድ ሙባረክ!

ጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ

ማህበረሰብን እንገነባለን!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *