በጊፍት ሪል ስቴት ስፖንሰርነት በተካሄደው የደም ለጋሾች ቀን ለተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ተሰጠ

የኢትዮጵያ ደምና ኅብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት መርሃ ግብሩ እውን እንዲሆን ጊፍት ሪል ስቴት ላደረገው ድጋፍ ልዩ ምስጋና አቅርቧል፡፡

በዕለቱ በመደበኝነት ደም ለሚለግሱና ለሚያስተባብሩ ግለሰቦች፣ የሐይማኖት ተቋማት፣ የበጎ አድራጎት ማኅበራት፣ የሚዲያ ተቋማት እንዲሁም ለሌሎችም አካላት እውቅና ተሰጥቷል።

ደም ማለት ሕይወት በመሆኑ ሕይወት እየሰጡ ለሚገኙ አካላት ምስጋና ይገባል ተብሏል።

አሁን ላይ ከፍተኛ የደም እጥረት በመኖሩ ሁሉም ደም በመለገስ ሕይወትን ሊያድን እንደሚገባ ተነስቷል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *