በጊፍት ሪልስቴት ስፖንሰርነት የሚካሄደው የባላገሩ ምርጥ የፍጻሜ ውድድር በመጪው እሁድ ፍጻሜውን ያገኛል፡፡

ላለፋት ሦስት ዓመታት ሲካሄድ የቆየው የባላገሩ ምርጥ የፊታችን እሑድ የካቲት 17/2016 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ፍፃሜውን ያገኛል።

ለአሸናፊዎች እስከ ስምንት ሚሊየን ብር ሽልማት ያዘጋጀው ባላገሩ ምርጥ ጊፍት ሪልስቴት አንደኛ የወጣውን ለመሸለም ስፖንሰር ያደረገ ሲሆን ከሚበረከተው ሽልማት ውስጥ 3 ሚሊየን ብሩ ለአልበም ዝግጅት እንደሚውል ታውቋል።

የፍፃሜ ተወዳዳሪዎቹ ስራዎቻቸውን በባላገሩ ቲቪ እና ዩ ቲዩብ ቻናል ቀጥታ ከሚሊኒየም አዳራሽ ያቀርባሉ።

በዕለቱ ከተመልካቾች ከትኬት ሽያጭ የሚገኘው የመግቢያ ዋጋ ለመቄዶንያ አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ይውላል።

በባላገሩ ምርጥ ለሦስት ዓመታት 2 ሺህ ተወዳዳሪዎች በተለያዩ ስራዎች ሲወዳደሩ መቆየታቸው ይታወሳል።

ጊፍት ሪልስቴት ለተወዳዳሪዎች ከወዲሁ ጥሩ የውድድር ጊዜ እንዲሆንላቸው ከወዲሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡

ጊፍት ሪል ስቴት

ማህበረሰብን እንገነባለን!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *