በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን እውቀት በስራ ላይ ስልጠና በተግባር ለመለወጥ ተግተው እንደሚሰሩ የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ የዩኒቨርስቲ ምሩቃን ሰልጣኞች ተናገሩ፡፡

በድርጅቱ የሚጠበቀው ውጤት እንዲመዘገብ የሁሉም ባለሙያ ቅንጅታዊ አሰራር ሊዳብር እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

ጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የቀጠራቸው ምሩቃን ሰልጣኞች የአንድ ወር የስራ ላይ ስልጠና ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በውይይቱም ሰልጣኞችም ለተሰጣቸው የስራ ላይ ስልጠና አመስግነው በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን እውቀት በስራ ላይ ስልጠና በተግባር ለመለወጥ ተግተው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡

በተቋማት ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣ በጥናት ላይ የተመሰረተ አሰራር እንደሚያስፈልግም ተነስቷል።

የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ የሰልጣኞች የስራ ላይ ስልጠና የአንድ ወር ሪፖርት በቀረበበት ወቅት እንደተናገሩት ሰልጣኞች በአንድ ወር ጊዜ ያሳዩት ለውጥ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም በስራ ላይ ተጨባጭ ውጤት እንዲመጣ ድርጅቱን በኔነት በማገልገል ጊዜና ጉልበታቸውን ያለስስት መጠቀም እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

ድርጅቱ በሀገር አቀፍ ብሎም በዓለም አቀፍ በሚፈለገው ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ከነባር ባለሙያዎች ልምድና እውቀትን በመቅሰም ጊዜን በአግባብ ወደስራ መተርጎም እንደሚያስፈልግም አቶ ገብረየሱስ አብራርተዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *